ቻይና በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያወጣቸው ጥብቅ ፖሊሲ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ያለውን አቅርቦት ሊጎዳ ይችላል - ባለሙያ
20:20 27.11.2025 (የተሻሻለ: 20:24 27.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ቻይና በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ ያወጣቸው ጥብቅ ፖሊሲ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት ያለውን አቅርቦት ሊጎዳ ይችላል - ባለሙያ
በቻይና በ"ዜሮ ኪሎ ሜትር" ያገለገሉ ተሽከርካሪ ምርቶች ላይ ከፍተኛ ጥገኛ የሆኑ አገራት በቤጂንግ አዲስ የቁጥጥር ስርዓት የውስጥ ገበያቸው የዋጋ መጨመር ሊገጥመው ይችላል ሲሉ የአውቶሞቲቭ አማካሪ የሆኑት ብሩክ አወቀ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
አዲሱ አሰራራ በገበያው የብቃት ማረጋገጫ፣ መለዋወጫ እና ዋስትና ያላቸው ምርቶች እንዲቀርቡ ቢያስችልም ከአጠቃላይ አቅርቦቱ 27 በመቶው በቻይና ምርቶች የተሞላው የኢትዮጵያ ገበያ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚበረታበት ያደርጋል ብለዋል ፡፡
“በኢትዮጵያ ከአምራቾች በቀጥታ ተሽከርካሪዎችን የሚያስመጡ ተቋማት ቁጥር ውስን ነው፤ በወኪልነት ከሚሰሩ ይልቅ ከነጋዴዎች ተረክበው ለገበያ የሚያቀርቡ በርካታ አስመጪዎች አሉ፡፡ስለዚህም አዲሱ ህግ ጥብቅ ቁጥጥር ስለሚያድርግ እና መስፈርቶችን ስለሚያስቀምጥ እነዚህ አስመጪዎች ተጽእኖ ያድርባቸዋል፤ ይህ ማለት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች አቅርቦት ሊቀንስና ዋጋዎችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡”
አዲሱ ደንብ፣ የቻይና ኩባንያዎችን ብራንድ ለመጠበቅና የገዢዎችን ዋስትና ለማረጋገጥ ወደ ውጭ የሚላኩ ተሽከርካሪዎች የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን እና ሌሎች ዝርዝሮችን የሚገልጽ "የዋስትና ማረጋገጫ ደብዳቤ" እንዲቀርብ ያስገድዳል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X