ጦርነቱ የሚቆመው የዩክሬን ወታደሮች ቦታዎቻቸውን ሲለቁ ነው - ፑቲን
16:52 27.11.2025 (የተሻሻለ: 17:04 27.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ጦርነቱ የሚቆመው የዩክሬን ወታደሮች ቦታዎቻቸውን ሲለቁ ነው - ፑቲን
በልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሁሉም አቅጣጫዎች ላይ አዎንታዊ ግስጋሴ መቀጠሉን እና የማጥቃት ፍጥነት እየጨመረ መሆኑን አስታውቀዋል።
የዩክሬን የጦር ኃይሎች በጥቅምት ወር 47 ሺ ወታደሮቻቸውን አጥተዋል ሲሉ ፑቲን ጠቁመዋል።
የጋራ ደህንነት ስምምነት ድርጅት በተመለከተም፤ ድርጅቱ ማንንም ስጋት ላይ አይጥልም፤ ሆኖም ማንኛውንም ጥቃት ለመመከት ዝግጁ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ፑቲን የሩሲያ የመከላከያ ኢንዱስትሪ በሰው አልባ አውሮፕላኖች ዘርፍ ያስመዘገባቸውን እድገቶች “አብዮት” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ሩሲያ በዓለም ላይ ትናንሽ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎችን የምትገነባ ብቸኛዋ ሀገር ነች ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል።
ሩሲያ እና ኪርጊስታን በጋራ ትናንሽ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ማቀዳቸውን አስታውቀዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X