ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏ ተገለፀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏ ተገለፀ
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏ ተገለፀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 27.11.2025
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት 4 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሏ ተገለፀ

አገሪቱ በበጀት ዓመቱ ለውጭ ባለሀብቶች የሰጠችው የኢንቨስትመንት ፈቃድ በ61 በመቶ ማደጉንም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ም/ኮሚሽነር ዳጋቶ ቁምቤ አስታውቀዋል።

"በ2016 በጀት ዓመት 326 ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ነበር። በ2017 ደግሞ ወደ 525 የሚጠጉ ባለሀብቶች በአገሪቱ ኢንቨስት ለማድረግ ፈቃድ ወስደዋል፣ ይህም ከፍተኛ ጭማሪ ያሳያል" ብለዋል።

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት መጨመር ቁልፍ ምክንያቶች፦

ሁሉን አቀፍ አገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መደረጉ፣

አገሪቱ ለኢንቨስትመንት ምኅዳር ያላትን አቅም ማስተዋወቅ በማቻሉ እና

ለኢንቨስትመንት ምቹ ያልሆኑ የአሠራር እና የሕግ ክፍተቶች በጥናት ተለይተው መሻሻላቸውንም ኃላፊው አረጋግጠዋል፡፡

መሰል እርምጃዎች የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ሥርዓትን ወደ ገበያ ተኮር መዋቅር ከመቀየር ጋር ተዳምረው፣ ለኢንቨስትመንትና ለንግድ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ አነቃቅተዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0