ቻይና ለአፍሪካ ያላት አቀራረብ ከአውሮፓውያን በተለየ መልኩ ሉዓላዊነትን የሚያከብርና የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታዎችን የማያካትት ነው - ተመራማሪ

ቻይና ለአፍሪካ ያላት አቀራረብ ከአውሮፓውያን በተለየ መልኩ ሉዓላዊነትን የሚያከብርና የፖለቲካ ቅድመ ሁኔታዎችን የማያካትት ነው - ተመራማሪ
የአውሮፓውያን "የአማካሪነት" አስተሳሰብ እሴቶችን የሚጭን እና የሰብአዊ መብቶች ሰበብ በማድረግ ማዕቀቦችን ይጥላል ሲሉ የሼጂያንግ ኖርማል ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ምርምር ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ሊዩ ቺንሃይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
ሊዩ እንዳሉት፣ የአውሮፓ ሕብረት ግሎባል ጌትዌይ የተባለው እቅድ በረጅም የግምገማ እና የማፅደቅ ሂደቶች ሲዘገይ፤ በቻይና የተገነቡ የመሠረተ ልማት አውታሮች፣ በተለይም የባቡር መስመሮች እና ወደቦች በፍጥነት ይጠናቀቃሉ እና የአፍሪካን ልማት በቀጥታ ይደግፋሉ፡፡
ቻይና በማኑፋክቸሪንግ እና በአዲስ ኢነርጂ ላይ ትኩረት በማድረግ በአፍሪካ ያላት ኢንቨስትመንት እየጨመረ ነው ያሉት ተመራማሪው የኢንዱስትሪ ልማትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን አነስተኛ ብድሮችን እና ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመጠቀም እንደምትከውን ተናግረዋል። በአንፃሩ፣ የአውሮፓ ሕብረት ተሳትፎ ብዙውን ጊዜ በሀብት ማውጣት ላይ በማተኮር ለኢኮኖሚያዊ ብዝኃነት የሚኖረው አስተዋፅኦ አነስተኛ ነው ሲሉ ሞግተዋል።
ቻይና ለአፍሪካ ፍላጎቶች ተስማሚ የሆኑ ተግባራዊ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና በአካባቢው ለሰለጠነ የሰው ኃይል ቅድሚያ ትሰጣለች ብለዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የቻይና የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሥራ ዕድል በመፍጠር እና ክህሎቶችን በማሳደግ ረገድ ምሳሌዎች መሆናቸውን የጠቆሙት ሊዩ የአውሮፓ ቴክኖሎጂዎች ግን ከአፍሪካ የልማት ደረጃ ጋር ብዙ ጊዜ ተመጣጣኝ አይደሉም ሲሉ አስረድተዋል።
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X