912 ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ስታዘዋውር የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ912 ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ስታዘዋውር የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች
912 ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ስታዘዋውር የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 26.11.2025
ሰብስክራይብ

912 ግራም በላይ አደንዛዥ እፅ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ስታዘዋውር የነበረች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

የ34 ዓመቷ ሙሊ አያን እንዱንጌ 3.6 ሚሊዮን ሺሊንግ (ከ28 ሺህ ዶላር በላይ) የሚያወጣ አደንዛዥ እጽ (ኮኬይን) ሆዷ ውስጥ በመያዝ ለማለፍ ስትሞክር በጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡

የኬንያ የፀረ-ዕፅ ክፍል መኮንኖች ከአዲስ አበባ ተነስታ ወደ ስፍራው ያቀናችውን ግለሰብ ከአውሮፕላኗ በወረደች ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረጉት ምርመራ ተጠርጣሪዋ እጽ የተሞላባቸው 28 እንክብሎችን ውጣ መገኘቷን የአገሪቱ ሚዲያ ዘግቧል፡፡

ፖሊስ በግለሰቧ ላይ ክስ ለመመሥረት መረጃዎችን እያደራጀ መሆኑን የገለፀ ሲሆን ዜጎች ከእፅ ዝውውር ራሳቸውን እንዲቆጥቡ አሳስቧል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0