የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ብዙ ርቀት ቀድሞ ተራምዷል - የናይጄሪያ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ

ሰብስክራይብ

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ ብዙ ርቀት ቀድሞ ተራምዷል - የናይጄሪያ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 

የኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳንጁማ አዳሙ ኢስማዒላ (ዶ/ር)፣ ዩኒቨርሲቲው ለአፍሪካውያን ወጣቶች የአቬዬሽን ሥልጠና መዳረሻ መሆን የሚያስችል አቅም መገንባቱን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

"ዩኒቨርሲቲው ለአፍሪካዊያን በጣም ጥሩ ዕድል እየሰጠ ነው። በብዙ  አገራት እንደልብ የማይገኙ ብዙ የሥልጠና መርሃ-ግብሮችም አሉት። ይህም አኅጉሪቱ በዘርፉ ለምትፈልገው የሰለጠነ የሰው ኃይል የላቀ እገዛ አለው።" ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ አፍሪካዊያን ወጣቶች ለአቬዬሽን ሥልጠና ወደ ሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚያደርጉትን ስደት ለመቀነስ በትብብር መሥራት እንደሚያስፈልግ አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0