የሱዳን ዳርፉር ክልል ገዥ በመጠለያዎች ካደረጉት ጉብኝት በኋላ አፋጣኝ ዕርዳታና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
18:09 26.11.2025 (የተሻሻለ: 18:14 26.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሱዳን ዳርፉር ክልል ገዥ በመጠለያዎች ካደረጉት ጉብኝት በኋላ አፋጣኝ ዕርዳታና ጥበቃ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
ሚኒ ሚናዊ በአል-ዳባ የሚገኘውንና ከኤል ፋሸር የተፈናቀሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሃን ዜጎች የተጠለሉበትን አል-አፋድ ካምፕ ጎብኝተዋል፡፡
ገዢው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ኤል ፋሸርን እና ሌሎች የዳርፉር አካባቢዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ ከደረሰው ጥቃት የሸሹት በመጠለያው ያሉ ነዋሪዎች በተለይም ሕጻናት፣ ሴቶች እና አረጋውያን የገጠማቸውን አስከፊ ሰብአዊ ሁኔታ በአካል ተገኝተው ተመልክተዋል።
የተሻለ ጥበቃ፣ ድጋፍና አስፈላጊ አገልግሎቶች እንዲያገኙ ጥሪ አቅርበው፣ ባለሥልጣናት የተፈናቀሉ ሰዎች በሰላም እና በክብር ወደየቤታቸው እንዲመለሱ ዝግጅት ማድረግ አለባቸው ብለዋል። በተጨማሪም ነዋሪዎች በሰላም ወደ ቤታቸው እስኪመለሱ ድረስ ዳርፉርን ከሚሊሻዎች ጥቃት ለመጠበቅ እና ነፃ ለማውጣት ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
ሚናዊ ሰብአዊ እርዳታ ላደረጉ ሱዳናውያን በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ዳርፉር አስተማማኝ እና የተረጋጋ እስክትሆን ድረስ ህዝቡን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X