በኤርታሌ አዲስ የተፈጠረው ከፍተኛ እሳተ ገሞራ ከሃይሊ ጉቢ ፍንዳታ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ተባለ
16:32 26.11.2025 (የተሻሻለ: 16:54 26.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በኤርታሌ አዲስ የተፈጠረው ከፍተኛ እሳተ ገሞራ ከሃይሊ ጉቢ ፍንዳታ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል ተባለ
ህዳር 16 ላይ የተነሳው የሴንቲነል-1 ሲንቴቲክ አፐርቸር ራዳር ምስል እንደሚያሳየው በአካባቢው የእሳተ ገሞራ እንቅስቃሴ ባይኖርም በኤርታሌ እሳተ ገሞራ ጫፍ ላይ 760 በ 350 ሜትር ስፋት ያለው አዲስ የመሬት ከፍታ መፈጠሩ ተገልጿል።
ይህ ክስተት በህዳር 14 በሃይሊ ጉቢ ከተከሰተው ኃይለኛ ፍንዳታ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል መባሉ ተዘግቧል፡፡
በዚህም ሁለቱ ጎረቤት የእሳተ ገሞራ ስርዓቶች ከመሬት በታች የሚቀልጥ አለት ማጠራቀሚያ እንደሚጋሩ እና ውስጣዊ የርስ በርስ ግፊት እንዳላቸው ያመላክታል ተብሏል።
የኤርታሌ ተራራማ አካባቢ አካል የሆነው የሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ፣ ቢያንስ ለ12 ሺ ዓመታት ያለእንቅስቃሴ ከቆየ በኋላ እሁድ ህዳር 14 ቀን ኃይለኛ እና ፍንዳታ የበዛበት እንቅስቃሴ ማሳየት መጀመሩ ተመላክቷል።

© telegram sputnik_ethiopia
/