ኢትዮጵያ ብሔራዊ የተመጣጠነ ምግብ መረጃ መድረክ የመጀመሪያ ምዕራፍን በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ
20:38 25.11.2025 (የተሻሻለ: 20:44 25.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ የተመጣጠነ ምግብ መረጃ መድረክ የመጀመሪያ ምዕራፍን በስኬት ማጠናቀቋ ተገለጸ
በአገሪቱ እያደገ የመጣው በመረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ ውሳኔ አሰጣጥ በሕጻናት የተመጣጠነ ምግብ እጦት ላይ በሚደረገው ትግል ትልቅ ውጤት እንዲመዘገብ አድርጎታል ሲሉ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው ቶሌራ መናገራቸውን የአገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል፡፡
“ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ የብሔራዊ የተመጣጠነ ምግብ መረጃ መድረክ ያስመዘገባቸውን አስደናቂ አስተዋፅዖዎች ከፍ ያለ ነው፤ ባለፉት ዓመታት ባሳካነው ነገር እጅግ እንኮራለን” ሲሉ የመረጃ አቅሙ በአገሪቱ የአመጋገብ ሁኔታ ላይ ያሳየውን እድገት ጠቅሰዋል።
በመጀመሪያው ምዕራፍ የተመዘገቡ የመረጃ ግኝቶች ወጤታማነት፦
የብሔራዊ የተመጣጠነ ምግብ ፕሮግራም ሁለትን ለመቅረጽ፣
ለምግብ ስትራቴጂ እና ለምግብ ስርዓት ሽግግር ፖሊሲ ግብዓትና
ለዋና ዋና አገራዊ ማዕቀፎች ቀጥታ መረጃ ምንጭ መሆን ችለዋል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X