- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የለውጥ ዋጋ ፡ ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምና ኢትዮጵያ

የለውጥ ዋጋ ፡ ዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋምና ኢትዮጵያ
ሰብስክራይብ
በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ የአለምዓቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍን) እና የኢትዮጵያን ግንኙነት፣ የኢኮኖሚ እድገት ዋሰትና ይሆን ወይስ የዕዳ ወጥመድ የሚለውን እንመረምራለን። ለዚህም ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና እና በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ጋብዘናቸዋል፡፡

እንደ ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት እና የወጪ ንግዳችን መጠን መጨመር ያሉ ትክክለኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጮች እስካልተፈጠሩ ድረስ፣ የውጭ ምንዛሪ ችግር ተፈቷል ልንል አንችልም። ሲሉ ከፍተኛ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ የለውጥ ዉጥኗን ለማሳካት ምን ማድረግ አለባት ?

ይህንን [በብድር የተገኘ] ገንዘብ በአገልግሎት ዘርፍ ላይ ማባከን አይገባም። [...]የኢኮኖሚውን ምርታማነትና የውጪ ንግድ አቅም ለማሳደግ በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና ዘርፎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይገባል። ሲሉ በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ ፡
አዳዲስ ዜናዎች
0