የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር እና አካላዊ ስጋቶችን ለመከታተል የሚያስችል ማዕከላዊ የደህንነት መቆጣጠሪያ ማዕከል ከፈተ
18:04 25.11.2025 (የተሻሻለ: 18:14 25.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር እና አካላዊ ስጋቶችን ለመከታተል የሚያስችል ማዕከላዊ የደህንነት መቆጣጠሪያ ማዕከል ከፈተ
በመላ አገሪቱ የሚገኙ ከ1920 በላይ የባንኩ ቅርንጫፎች እንቅስቃሴን በቀጥታ የካሜራ ክትትል ከማዕከሉ ለመቆጣጠር ያለመ መሆኑን በባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ኤፍሬም መኩሪያ ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
ባንኩ ያስጀመረው ማዕከል፡-
◼ የአሰራር ቁጥጥር ለማድረግ፣
◼ ደህንነት ለማጠናከር፣
◼ ጥሰቶችን ለመከላከል እና
◼ ችግሮች ሲያጋጥሙ አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ የ24/7 አገልግሎት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።
ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር በባንኩ ላይ ባጋጠመው የሲስተም ችግር ደንበኞች በሂሳባቸው ውስጥ ከነበራቸው በላይ ገንዘብ እንዲያወጡ አልያም እንዲያስተላልፉ በማስቻል ከ801 ሚሊዮን ብር በላይ አደጋ ላይ ወድቆ እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X