- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

የማይታይ ሞተር ፡ የአፍሪካ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ

የማይታይ ሞተር ፡ የአፍሪካ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ
ሰብስክራይብ

“እነዚህ ኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የምንላቸው ዋነኛ ቀጣሪ ሴክተር ናቸው፤ መተዳደሪያም ነው፤ ኢኮኖሚው የተረጋጋ እነዲሆን ያደርጋል፡፡ ኢኮኖሚውን በማረጋጋት ደረጃ የተለያዩ ነገሮች ለዝቅተኛ ማህበረሰብ በማቅረብ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ ነው፡፡“ ሲሉ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የኢ-መደበኛ ኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ለስራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚው ያለውን አስተዋጽዎ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚክስ ማህበር ውስጥ ተመራማሪ ዘነበች አድማሱ (ዶ/ር) ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡ በተጭማሪም ስለ ኢትዮጵያ የማሪታይም ትምህርት በኢትዮጵያ ባህር ትራስፖርት እና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን የባቦጋያ ማሪታይም እና ሎጅስቲክስ አካዳሚ ዲን ከአቶ ሲራጅ አብዱላሂ ጋር ያደረግነው ውይይት በዚህ ዝግጅት ውስጥ ተካቷል፡፡

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡
አዳዲስ ዜናዎች
0