ዲቦራ ፋውንዴሽን አገልግሎቱን ወደ ክልሎች ለማስፋት አየሠራ መሆኑን አስታወቀ

ሰብስክራይብ

ዲቦራ ፋውንዴሽን አገልግሎቱን ወደ ክልሎች ለማስፋት አየሠራ መሆኑን አስታወቀ

በመላ አገሪቱ የሚገኙ የአዕምሮ ዕድገት ዉሱንነት ያለባቸው ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና ክብካቤ እንዲያገኙ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የፋውንዴሽኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቤኪ አባዱላ ገልጸዋል።

ዋና ሥራ አስኪያጇ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣  ፋውንዴሽኑ የሕፃናቱን መብት አና ጥቅም በማስከበር በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን መተለሙንም ተናግረዋል።

"ዳውን ሲንድሮም፣ ኦቲዝም፣ ሴሬብራል ፓልሲ እና ሌሎች የአዕምሮ ዕድገት  ዉሱንነት እና የእንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ከ2 ሺህ በላይ ሕፃናት የጤና፣ የትምህርት እና የፖሊሲ ማንቃት ድጋፍ እያደረግን ነው። አገልግሎታችንን ወደ ገጠር አካባቢዎች ለማስፋትም እየሠራን ነው።" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0