የሕንዱ ማላባር ጎልድ ኤንድ ዳይመንድስ "ከረሃብ የጸዳ ዓለም" የተሰኘ ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያ ሊያስጀምር ነው
16:29 25.11.2025 (የተሻሻለ: 16:34 25.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሕንዱ ማላባር ጎልድ ኤንድ ዳይመንድስ "ከረሃብ የጸዳ ዓለም" የተሰኘ ፕሮጀክቱን በኢትዮጵያ ሊያስጀምር ነው
ፕሮጀክቱን ለማስጀመር የሚያስችል ይፋዊ ፍላጎት ማሳወቂያ ደብዳቤን የማላባር ግሩፕ ምክትል ሊቀመንበር አብዱል ሰላም ኬ.ፒ. በዱባይ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ለሆኑት አስመላሽ በቀለ አስረክበዋል።
“ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ከ864 ሺ ዶላር በላይ ኢንቨስት እናደርጋለን። ግባችንም እስከ 2026 መጨረሻ ድረስ ለ10 ሺ ሕጻናት በየቀኑ ምግብ ማቅረብ እና የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ መሠረተ ልማትን ማካሄድ ነው” ሲሉ የማላባር ግሩፕ ሊቀመንበር ኤም.ፒ. አሀመድ አስታውቀዋል።
የፕሮጀክቱ የመጀመሪያ ምዕራፍ በኦሮሚያ ክልል፣ አዳማ ከተማ በሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ወደ 11 ሺ የሚጠጉ ሕጻናትን በማቀፍ እንደሚጀምር ተመላክቷል።
ፕሮጀክቱ ፦
▫ የትምህርት ዕድሎች፣
▫ የማማከር እና ክትትል ፕሮግራሞች፣
▫ የዲጂታል እውቀት ስልጠና፣
▫ የቤተ-መጻሕፍት ልማት እና ሌሎችንም ያካትታል።
ከ"ረሃብ የጸዳ ዓለም" ፕሮግራም የተቋሙ የማኅበራዊ ኃላፊነት ተነሳሽነቶች አካል ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ 119 አካባቢዎች በየቀኑ ከ115,000 በላይ ምግቦችን እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X