- Sputnik አፍሪካ, 1920
The Rising South
የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ፡ ለአፍሪካ ንግድ አዲስ ምዕራፍ

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ፡ ለአፍሪካ ንግድ አዲስ ምዕራፍ
ሰብስክራይብ

“የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና መመስረት [...]ይህ ለአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ ለመነገድ ዕድል ይሰጣል። እስከ አሁን ድረስ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው ንግድ 15 በመቶ ብቻ ነው። የአፍሪካ ሀገራት ያለ ቀረጥ እንዲነግዱም ዕድል ይሰጣል።” ሲሉ የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና የትግበራ ዝግጅትን ተከትሎ ከፍተኛ ኢኮኖሚስት ቆስጠንጢኖስ በርኸተስፋ (ዶ/ር) ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀናቸዋል። በዚሁ ዝግጅታችን ፣ እ.ኤ.አ ጥቅምት 7 ፣ 2025 ሁለተኛ ዓመቱ የደፈነውን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭት መነሻ አድርገን ፣ ስኬት የምዕራብ ዓለም መራሹን ድርድሮችና ለውድቀታቸው ምክንያት የሆኑ ነጥቦች እንዲሁም እያደገ የመጣው የባለብዙ-ዋልታ ዓለም አማራጭ የአሸማጋይነት ሚና በተመለከተ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ መሀመድ ኢብራሂም ምሁራዊ ምልከታዎችን ጠይቀናቸዋል።
ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፐሮግራሙን ያዳምጡ፡
አዳዲስ ዜናዎች
0