ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 25.11.2025
ሰብስክራይብ

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የሚያደርገውን ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅርና መሰል ተግባራትን ያካተተ ውስጣዊ ግምገማ በማድረግ ውጤቱን ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን የተቋሙ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለአገር ውስጥ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡

ይህን ተከትሎ ተቋሙ ከትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሠረት የራስ ገዝነት አሠራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያድርግ ገልፀዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በምርምርም፣ በመማር ማስተማር፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና በማኅበረሰብ አገልግሎት ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ ለመዝለቅ የሚያስችል የተሟላ ዝግጅት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0