ሙሴቬኒ እና ሩቶ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት እና የክልሉን የኢንዱስትሪ ዕድገት ይደግፋል የተባለ አዲስ የብረታብረት ፋብሪካ በኡጋንዳ ሥራ አስጀመሩ
19:15 24.11.2025 (የተሻሻለ: 20:14 24.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሙሴቬኒ እና ሩቶ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት እና የክልሉን የኢንዱስትሪ ዕድገት ይደግፋል የተባለ አዲስ የብረታብረት ፋብሪካ በኡጋንዳ ሥራ አስጀመሩ
በምስራቅ ኡጋንዳ ቶሮሮ ከተማ ውስጥ የተገነባው የዴቭኪ ብረታብረት ፋብሪካ "አፍሪካን ለዘመናት ከዘለቀው ብዝበዛ ነጻ ለማውጣት" ወሳኝ እርምጃ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ ተናግረዋል።
"ከ500 ዓመታት በላይ በባርነት፣ በቅኝ ግዛት እና ወደ ውጭ በሚላኩ ጥሬ ዕቃዎች የተነሳ እሴት ስናጣ ቆይተናል" ሲሉ አብራርተዋል።
አዲሱ ፋብሪካ ለ15 ሺህ ኡጋንዳውያን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ሙሴቬኒ አመልክተዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ "ይህ ለውጥ አምጪ ኢንቨስትመንት ለኡጋንዳ ብቻ ሳይሆን ለኬንያ እና ለክልሉ የሚያገለግል ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የኬኒያው መሪ አክለውም የዴቭኪ ብረታብረት ፋብሪካ፦
አዳዲስ የእሴት ሰንሰለቶችን በመፍጠር፤
የገቢ ንግድ ወጪን በመቀነስ፣
አዳዲስ ዕድሎችን በማቅረብ ጥቅም እንደሚያስገኝ ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


