ታንዛኒያ በመጪው ታህሳስ ግዙፍ የወደብ ግንባታ ልታስጀምር ነው
18:15 24.11.2025 (የተሻሻለ: 18:24 24.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታንዛኒያ በመጪው ታህሳስ ግዙፍ የወደብ ግንባታ ልታስጀምር ነው
የሀገሪቱ መንግሥት ዋና ቃል አቀባይ ገርሰን ምሲግዋን በመጥቀስ የምዕራቡ ዜና ማሰራጫ እንደዘገበው፤ የባጋሞዮ ወደብ እስከ 20 ሜትር ጥልቀት የሚኖረው ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ወደቦች በበለጠ ትላልቅ መርከቦችን የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል፡፡
"ወደቡ እስከ 25 ሺህ ኮንቴይነሮች የመያዝ አቅም ያላቸው መርከቦችን ማስተናገድ ይችላል" ብለዋል፡፡
የባጋሞዮ ወደብ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ከትራንስፖርት ግንኙነቶች ጋር የተያያዘ የግዙፍ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አካል ነው ሲል የዜና ማሰራጫው ዘግቧል፡፡
ግንባታው እ.ኤ.አ በ2013 በውጭ አልሚዎች ተፈርሞ የነበረውን ስምምነት የሀገሪቱ መንግሥት መቃወሙን ተከትሎ ለአስርት ዓመታት የተፈጠረውን መዘይገት ይቋጫል፡፡
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለፀገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X