ሞሮኮ የ2025 ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ተብላ ተሰየመች
17:29 24.11.2025 (የተሻሻለ: 17:34 24.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሞሮኮ የ2025 ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ተብላ ተሰየመች
ሞክሮ ይህንን ክብር ያገኘችው በብራስልስ በተካሄደው እና ወደ አንድ ሺህ የሚጠጉ የቤልጂየም የቱሪዝም ባለሙያዎች በተገኙበት በ25ኛው የ2025 የጉዞ ሽልማት ላይ ነው።
ስኬቱ ከፍተኛ ባሕላዊ ቅርስ እና በዘርፉ በዘላቂነት ኢንቨስት የምታደርገው ሞሮኮ፤ ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻ መሆኗን አጉልቷል።
ሞሮኮ እስካሁን ከ16 ሚሊዮን በላይ ቱሪስቶችን ያስተናገደች ሲሆን በታህሳስ መጨረሻ 18 ሚሊዮን ቱሪስቶች እንደሚጠበቁ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
መንግሥት እ.ኤ.አ በ2026 ዕደገቱን ለማስቀጠል፤ ዓለም አቀፍ የማስተዋወቅ ሥራን በማጠናከር የሚያቀርባቸውን አማራጮች ለማስፋት እና ባለሀብቶችን ለመደገፍ አቅዷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X