- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል።አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ነጻ ማውጣት፦ በንጉጊ ዋ ቲዮንጎ እይታ

የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ነጻ ማውጣት፦ በንጉጊ ዋ ቲዮንጎ እይታ
ሰብስክራይብ

"እኛ ደግሞ አፍሪካውያኖች የራሳችን ታሪክ የምንነግርበት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናስተላልፍበት ጥበብ፣ የራሳችን መንገድ አለን። ስለዚህ ይሄ የአውሮፓ ተኮር የሆነውን አመለካከት ከአፍሪካ ስነ ጽሁፍ ውስጥ አውጥተን በአፍሪካ ተኮር ወይም ደግሞ አፍሮ ሴንትሪክ በሆነው ስንተካ አንደኛ ዲኮሎናይዝ እያደረግን ነው ማለት ነው።" - ሲሉ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋና ስነጽሁፍ መምህር እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ፣ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ስነጽሁፍ አስተማሪ እና በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነሰብ ኮሌጅ ዲን አስቻለው ለገሰን (ዶ/ር) አነጋግሮ የአፍሪካን ስነጽሁፍ ከቅኝ ግዛት እሳቤ ለማላቀቅ መደረግ ያሉባቸውን ጉዳዮች በቀዳሚው ክፍል እናስደምጣችኋለን። እንዲሁም ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረክ መለያ የሆኗትን አትሌቲክስ (አትሌቶቿን) እና ቡናን በዲፕሎማሲ ረገድ ''ሶፍት ዲፕሎማሲ'' አማራጭነት መጠቀም በምትችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሁለተኛው ጉዳያችን አድርገነዋል። ለዚህም የታሪክ አጥኝ እና የመገናኛ ብዙሀን ጥናት ባለሞያ የሆኑትን ተረፈ ወርቁን አነጋግረናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:
አዳዲስ ዜናዎች
0