ግብፅ በዓለም አቀፍ አርኪኦሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ግኝቶች ይፋ ለማድረግ ዝግጁ ናት - የአርኪኦሎጂ ምሁር
16:55 24.11.2025 (የተሻሻለ: 17:04 24.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ግብፅ በዓለም አቀፍ አርኪኦሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ግኝቶች ይፋ ለማድረግ ዝግጁ ናት - የአርኪኦሎጂ ምሁር
የሩሲያ የግብፅ ጥናት ምሁር ቪክቶር ሶልኪን ለስፑትኒክ እንደተናገሩት፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ13ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው እና በሶሃግ ግዛት፣ አኽሚም ውስጥ የሚገኘው የታላቁ ራምሴስ ሁለተኛ ዘመን ቤተ-መቅደስ እሳካሁን አልተቆፈረም።
ሶልኪን “በሂደት ግብፅ የገንዘብ ድጋፍ ስታገኝ እና የተወሰነ የከተማው ክፍል በአቅራቢያው ወደሚገኝ ምቹ ቦታ ሲዛወር፤ በራምሴስ ሁለተኛ ዘመን የነበረውን ሙሉ በሙሉ ያልተነካ ቤተመቅደስ እናያለን” ብለዋል።
ራምሴስ ሁለተኛ ከጥንቷ የግብፅ ታላላቅ ገዥዎች አንዱ ሲሆኑ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከ60 ዓመታት በላይ ሀገሪቷን ገዝቷል። ገዥው ግብፅን ለታላላቅ ወታደራዊ ድሎችና የግዛት መስፋፋት መርተዋል ሲሉ ሶልኪን አክለዋል።
ሁሉም የዘመናዊ ሥነ-ጽሑፍ ክላሲካል ዘውጎች ከጥንቷ ግብፅ የሚመዘዙ ናቸው። በተጨማሪም ለዘመናዊ ሕክምና መሠረት በመጣል ግሪክን፣ ሮምንና አውሮፓን በሰፊው እንዳነሳሳች ሶልኪን ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X