ሲንጋፖር በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ኤምባሲዋን ኢትዮጵያ ውስጥ ልትከፍት ነው

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሲንጋፖር በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ኤምባሲዋን ኢትዮጵያ ውስጥ ልትከፍት ነው
ሲንጋፖር በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ኤምባሲዋን ኢትዮጵያ ውስጥ ልትከፍት ነው - Sputnik አፍሪካ, 1920, 24.11.2025
ሰብስክራይብ

ሲንጋፖር በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ ኤምባሲዋን ኢትዮጵያ ውስጥ ልትከፍት ነው

የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ አዲሱ ኤምባሲ ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርገው አጋርነት ቁርጠኛ እንደሆነች እንዲሁም በሀገሪቱ ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት እና እምቅ አቅም እምነት እንዳለት "ተጭባጭ ማሳያ" ነው ብለዋል፡፡

“አዲስ አበባ መገኘታችን ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በተሻለ ሁኔታ ግንኙነት እንድንፈጥር፣ ስለ አፍሪካ ያለንን ግንዛቤ እንድናሰፋ እና አዳዲስ የትብብር ዘርፎችን እንድንቃኝ ያስችለናል” ብለዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2027 ይከፈታል ተብሎ የሚጠበቀው ኤምባሲ ለሲንጋፖር፤ ከግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጥሎ በአኅጉሪቱ ሦስተኛው የዲፕሎማሲ ቢሮ ይሆናል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ እና ሲንጋፖር በክህሎት ልማት እና በካርበን ብድር ትብብር ዙሪያ ዛሬ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቶቹ “ጽኑ እና ለነገው ገበያ ዝግጁ የሆኑ ሠራተኞችን ለማፍራት ብሎም በአየር ንብረት ጥበቃ ረገድ ዘላቂ፣ ዝቅተኛ ካርበን የሚያወጣ እድገት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ አቋም የሚያንፀባርቅ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ገፃቸው ፅፈዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0