ደቡባዊው ዓለም የራሱ ቦታ አለው - 'ጉልበተኞች እንዲነካኩን አንፈቅድም' - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

ደቡባዊው ዓለም የራሱ ቦታ አለው - 'ጉልበተኞች እንዲነካኩን አንፈቅድም' - የደቡብ አፍሪካ ሚኒስትር

የደቡብ አፍሪካ የግብርና ሚኒስትር ጆን ስቲንሃውስን የቡድን 20 መግለጫን "እውነተኛ የስኬት አክሊል" ሲሉ በማሞገስ፤ የምግብ ዋስትና፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ዓለም አቀፍ ግፊቶችን የመቋቋም አቅም ላይ ጠንካራ ትኩረት መስጠቱን ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለመጠይቅ ተናግረዋል።

በመግለጫው አምስት ግብርናን የተመለከቱ አንቀፆች መኖራቸውን እና የደቡብ አፍሪካ "ኡቡንቱ" የከፍተኛ ደረጃ የምግብ ዋስትና ሂደትን ጠቅሰው፤ “በምግብ ዋስትና እና በብሔራዊ ደኅንነት መካከል የማይነጣጠል ትስስር አለ” ሲሉም አጽንዖት ሰጥተዋል።

የተረጋጋ የምግብ ሥርዓትን ማረጋገጥ ዜጎችን በዓለም አቀፍ ግጭቶች እና በገበያ መዋዠቅ ከሚፈጠሩ መናጋቶች ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ስቲንሃውስን የቡድን 20 መግለጫ ቀድሞ መጽደቁ “ሥራውን በቁም ነገር የሚመለከት የቡድን 20” መሆኑን የሚያሳይ ግልጽ ምልክት ነው ብለዋል።

ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ ጋር ያላት የግብርና ትስስር ውስን መሆኑን በማንሳትም፤ በተለይ ሀገሪቱ ገለልተኝነቷን በምታጠናክርበት በዚህ ወቅት ትብብሩ ማደግ እንደሚችል እምነታቸውን ገልፀዋል።

አፍሪካ ባላት የተፈጥሮ ሀብት፣ የግብርና አቅም፤ ለሀገራት መረጋጋት፣ ለተሃድሶ እና ለዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ቁርጠኛ ከሆነች “የዓለም የዳቦ ቅርጫት” መሆን እንደምትችል ተናግረዋል።

የውጭ ጫናን አስመልክቶ ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ሰው የሚነካካህ አንተ ስትፈቅድ ብቻ ነው።...እኛ (ደቡባዊው ዓለም) በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ቦታ አለን ቦታችንንም እንይዛለን።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0