አርጀንቲና የመጨረሻውን የቡድን 20 መግለጫ ውድቅ አደረገች

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱአርጀንቲና የመጨረሻውን የቡድን 20 መግለጫ ውድቅ አደረገች
አርጀንቲና የመጨረሻውን የቡድን 20 መግለጫ ውድቅ አደረገች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 23.11.2025
ሰብስክራይብ

አርጀንቲና የመጨረሻውን የቡድን 20 መግለጫ ውድቅ አደረገች

አርጀንቲና የቡድን 20 መግለጫ ዋነኛ መሠረት የሆነው የስምምነት መርህ "ተጥሷል" ብላለች። ሀገሪቱ መግለጫው የእራሷን ጨምሮ የሁሉንም አባላት ስምምነት ሳያገኝ በመፅደቁ እንዳዘነች ገልፃለች።

ብዌኖስ አይረስ በተለይም በመካከለኛው ምስራቅ ግጭት ላይ መሠረታዊ አለመግባባቶች አንስታለች። አርጀንቲና ሰነዱ "ከፊል" እይታን በማቅረብ ለፍትሐዊ፣ ዘላቂና ሚዛናዊ ሰላም አስፈላጊ ናቸው ያለቻቸውን የክልላዊ ሁኔታዎችና መሠረታዊ መዋቅራዊ ምክንያቶችን አለማካተቱን ጠቅሳ ሞግታለች።

ደቡብ አፍሪካ በበኩሏ የአርጀንቲና ሰነዱን አለመቀበል የተለመደ አድርጋ እንደምትመለከተው የሀገሪቱ መንግሥት ፕሬስ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ዊሊያም ባሎይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

"አርጀንቲና ተቃውሞ ያቀረበች ብቸኛዋ ሀገር ናት" በማለት፤ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረገው ጥረት በቀጣይ የቡድን 20 ጉባኤዎች ሊቀጥል እንደሚችል አክለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0