'የሳሕል ጥምረት ሀገራትን በተመለከተ ብዙ የተሳሳተ መረጃ አለ' - የማሊ የግብርና ሚኒስትር
10:09 23.11.2025 (የተሻሻለ: 10:14 23.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
'የሳሕል ጥምረት ሀገራትን በተመለከተ ብዙ የተሳሳተ መረጃ አለ' - የማሊ የግብርና ሚኒስትር
ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን የሳሕል ሀገራትን በአሉታዊ መልኩ ያቀርባሉ፤ እንዲህ ያሉ ድርጊቶች ደግሞ ዓለም አቀፍ አጋርነቶችን ያደናቅፋሉ ሲሉ ዳንኤል ሲሜዮን ኬሌማ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል።
ኬሌማ "ይህን የተሳሳተ መረጃ ለመቋቋም የሚያስችለንን ማንኛውንም ዘዴ ለመከተል ዝግጁ ነን" በማለት፤ የሐሰት ዜናዎችን ከአካባቢው ፕሬሶች ጋር በመተባበር የሚታገሉ አማራጭ የሚዲያ ተቋማትን ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የውሸት ትርክቶች ውጫዊ ግንዛቤዎች ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድሩ ቢችሉም፤ የማሊ ዜጎች የምዕራባውያን ሚዲያ ሪፖርቶችን ማመን አቁመዋል ሲሉም አፅንዖት ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ እውነተኛ ዘገባን መመለስ አጋሮችን ለመሳብ እና የሳሕልን እውነተኛ ዕድሎች ለማሳየት እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X