ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹ ቁጥር 86.1 ሚሊዮን መድረሱን አስታወቀ
19:35 22.11.2025 (የተሻሻለ: 19:44 22.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹ ቁጥር 86.1 ሚሊዮን መድረሱን አስታወቀ
ኩባንያው በ2013 የቴሌብር አገልግሎትን ወደ ሥራ ካስገባ ጀምሮ 57.59 ሚሊዮን ደንበኞችን በማፍራት፣ 6.18 ትሪሊዮን ብር የሚያወጡ 2.61 ቢሊዮን ያህል ግብይቶችን ማስተናገዱን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አራት ዓመታት በዲጂታል ዘርፍ፦
ከ15 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች በማፍራት 31.64 ቢሊዮን ብር ብድር አቅርቧል።
4.71 ሚሊዮን ደንበኞቹ 30.32 ቢሊዮን ብር ቆጥበዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ የደንበኞቹን ቁጥር 88 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን መግለፁ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X