ቡድን 20 የአንድ ሀገር ድምፅ ሳይሆን የሁሉም ነው፤ ደቡብ አፍሪካ ምንም እንኳ አሜሪካ ግፊት ብታደርግም በጉባኤው መግለጫ ፅኑ አቋም አላት - ቃል አቀባይ

ሰብስክራይብ

ቡድን 20 የአንድ ሀገር ድምፅ ሳይሆን  የሁሉም ነው፤ ደቡብ አፍሪካ ምንም እንኳ አሜሪካ ግፊት ብታደርግም በጉባኤው መግለጫ ፅኑ አቋም አላት - ቃል አቀባይ

የቡድን 20 አባል ሀገራት ከአንድ ዓመት በላይ የሠሩት የጋራ ሥራ በመጨረሻ ደቂቃ ሊሻር አይችልም ሲሉ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ቃል አቀባይ ቪንሰንት ማግዌኒያ ከድርጅቱ ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

"ሀገራት ለዚህ ሂደት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። አሜሪካ በመጨረሻው ሰዓት መጥታ ሀገራት የመግለጫው አካል መሆን የለባቸውም ወይም መግለጫውን መደገፍ የለባቸውም ስትል፤ ትርጉሙ እነዚህ ሁሉ ሀገራት ዓመቱን ሙሉ ያደረጉትን ኢንቨስትመንት ወደ ጉን ይበሉ ማለት ነው" ብለዋል።

የቡድን 20 ስኬት የአስተናጋጇ ሀገር ብቻ ሳይሆን ሁሉንም አባል ሀገራት፣ ዜጎቻቸውን እና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን እንደሚጠቅም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ማግዌኒያ በደቡብ አፍሪካ እና በአሜሪካ መካከል የተፈጠረው የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ውጥረት “በምንም መልኩ የቡድን 20ን ሥራ ማበላሸት ወይም አደጋ ላይ መጣል የለበትም” ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0