የአሜሪካ ጄኔራሎች በትራምፕ የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ሩሲያ ሊያመሩ መሆኑ ተዘገበ
15:04 22.11.2025 (የተሻሻለ: 15:14 22.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የአሜሪካ ጄኔራሎች በትራምፕ የዩክሬን የሰላም ዕቅድ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ሩሲያ ሊያመሩ መሆኑ ተዘገበ
በሠራዊቱ ሴክሬታሪ ዳን ድሪስኮል የሚመራ ከፍተኛ የአሜሪካ ወታደራዊ ባለሥልጣናት ልዑክ በሚቀጥለው ሳምንት መጨረሻ ወደ ሩሲያ ሊበር ይችላል ሲል ዘ ጋርዲያን ዘግቧል።
የልዑካን ቡድኑ ሐሙስ በዩክሬን ከዘለንስኪ ጋር ውይይት አድርጓል። ትራምፕ ድሪስኮልን ለዩክሬን የሰላም ድርድር አዲሱ “ልዩ ተወካያቸው” አድርገው ሰይመዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ስምምነቱን እንዲፈርም ህዳር 18 ቀን "ተገቢ ጊዜ" እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
“ሊቀበለው ይገባል…በሆነ ወቅት የሆነ ነገር ለመቀበል ይገደዳል” ሲሉ ትራምፕ ስለ ዘለንስኪ ተናግረዋል።
አሜሪካ ዩክሬን ስምምነቱን ካልፈረመች የደህንነት መረጃ መጋራት አልያም የሎጂስቲክ ድጋፍን ልታቋርጥ ትችላለች በሚሉ ዘገባዎች መካከል አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ይህንን ብለዋል፡፡
“ዩክሬን የሰላም ስምምነት ላይ እንድትደርስ ከአሜሪካ ጠንካራ ፍንጭ ተሰጥቷታል። ማንኛውም ለውጦች የሚወሰኑት በፕሬዝዳንቱ በራሳቸው ይሆናል”።
ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ የትራምፕን የሰላም ዕቅድ በጽሑፍ እንዳገኘች እና ለሰላም ንግግሮች ዝግጁ እንደሆነች ገልፀዋል። የእቅዱ ዝርዝር ጉዳዮች ውይይት እንደሚያስፈልጋቸውም ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X