ሩሲያ ፈጣን የዴንጊ ትኩሳት መመርመሪያ መሳሪያ ማበልፀጓን የሀገሪቱ ጤና ኤጀንሲ አስታወቀ
14:20 22.11.2025 (የተሻሻለ: 14:24 22.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያ ፈጣን የዴንጊ ትኩሳት መመርመሪያ መሳሪያ ማበልፀጓን የሀገሪቱ ጤና ኤጀንሲ አስታወቀ
በሩሲያ የጤና ኤጀንሲ ሮስፖትሬብናድዞር የተሠራው ይህ የምርመራ መሳሪያ፤ የዴንጊ ቫይረስን ከ30-35 ደቂቃ ውስጥ በመለየት በተለምዶ በርካታ ሰዓታት ከሚፈጀው የፒሲአር ምርመራ በእጅጉ ፈጣን መሆኑን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ሮስፖትሬብናድዞር መሳሪያው የበሽታውን ሁኔታ በፍጥነት ለመለየት፣ ተገቢውን ህክምና ለመስጠት እና አስፈላጊ የፀረ-ወረርሽኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ ያስችላል ብሏል።
የዴንጊ ትኩሳት የመጀመሪያ ምልክቶች ከመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን ጋር ስለሚመሳሰሉ ልዩ የምርመራ ተግዳሮቶችን የሚፈጥር ሲሆን በሽታው የሚሰራጨው ደግሞ በሐሩር ክልል በሚገኙ ትንኞች አማካኝነት ነው።
እንደ ሮስፖትሬብናድዞር ገለጻ፤ አዲሱ ምርመራ ለዚህ አጣዳፊ ተላላፊ የቫይረስ ኢንፌክሽን ትክክለኛ እና ፈጣን ምርመራ ከማደርግ አኳያ የነበረውን ክፍተት ይሞላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X