የፈረንሳይ ባንኮች ለአማዞን ደን ምንጠራ ተጠያቂ የሆኑ ግዙፍ የአኩሪ አተር ኩባንያዎችን ፋይናንስ በማድረግ ተከሰሱ
11:18 22.11.2025 (የተሻሻለ: 11:24 22.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የፈረንሳይ ባንኮች ለአማዞን ደን ምንጠራ ተጠያቂ የሆኑ ግዙፍ የአኩሪ አተር ኩባንያዎችን ፋይናንስ በማድረግ ተከሰሱ
ሬክሌም ፋይናንስ እና ካኖፒ የተሰኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዳስታወቁት፤ አራት ታላላቅ የፈረንሳይ ባንኮች መሬት በመውረር ለአማዞን ደን መመንጠር አስተዋፅዖ አድርገዋል ተብለው ለተከሰሱት ባንጌ እና ካርጊል የግብርና ኮርፖሬሽኖች የ10 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ዝውውር አመቻችተዋል።
ድርጅቶቹ፤ ቢኤንፒ ፓሪባስ፣ ሶሲየት ጄኔራል፣ ክሬዲት አግሪኮል እና ባንክ ፖፑላየር ካይሴ ዲ'ኤፓርኝን "በደን መጨፍጨፍ ላይ ደካማ ወይም ፈፅሞ የሌሉ ፖሊሲዎችን" በመከተል ነቅፈዋል።
መንግሥታዊ ያልሆኑት ድርጅቶቹ፤ በአማዞን እ.አ.አ ከ2018 እስከ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ከአኩሪ አተር ጋር የተያያዘው የደን መጨፍጨፍ በሦስት እጥፍ መጨመሩ፤ የደን ሥነ-ምህዳሩን ለመጠበቅ ይበልጥ ጠንካራ የባንክ ደንቦች በአስቸኳይ እንደሚያስፈልጉ ማሳያ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X