ደቡብ አፍሪካ በቡድን 20 መግለጫ እና በደቡባዊ ዓለም ቅድሚያ ጉዳዮች ላይ ጽኑ አቋም አላት - ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ በቡድን 20 መግለጫ እና በደቡባዊ ዓለም ቅድሚያ ጉዳዮች ላይ ጽኑ አቋም አላት - ባለሥልጣን

አሜሪካ እንዳይወጣ ጫና ብታደርግም ፕሬቶሪያ የቡድን 20 መሪዎችን መግለጫ በእቅዱ መሠረት ታቀርባለች ሲሉ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ምክትል ቃል አቀባይ ዊሊያም ባሎይ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልፀዋል።

ከ2024 ጀምሮ የቡድኑን ፕሬዝዳንትነት ይዛ የቆየችው ሀገሪቱ፤ በስምምነት ላይ ለተመሰረቱ ውጤቶች ቅድሚያ እንደምትሰጥ እና በአብሮነት፣ በዘላቂነት፣ በዕዳ እፎይታ፣ በኢነርጂ ሽግግር እና በሰብዓዊ መብቶች ላይ ትኩረት እንደምታደርግ ከጉባዔው ጎን ለጎን ተናግረዋል።

“እንደምታውቀው ቡድን 20 የትልልቅ ኢኮኖሚዎች ስብስብ ነው፤ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ከአነስተኛ ኢኮኖሚዎችም ጋር አብራ ትቆማለች፡፡ የምናቀርበው ራዕይ በመሪዎቹ እንደሚንጸባረቅ ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ቃል አቀባዩ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0