ሱዳን በድህረ-ጦርነት መልሶ ግንባታ ወቅት በሩሲያ እርዳታ ትተማመናለች- በተመድ የሱዳን ቋሚ መልዕክተኛ
10:38 22.11.2025 (የተሻሻለ: 10:44 22.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳን በድህረ-ጦርነት መልሶ ግንባታ ወቅት በሩሲያ እርዳታ ትተማመናለች- በተመድ የሱዳን ቋሚ መልዕክተኛ
"ሩሲያ የሱዳን እውነተኛ ወዳጅ እና አጋር ናት፤ በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ፍላጎቶች የሌላት ሀገር ናት። ሩሲያ ሁልጊዜም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርሆዎችን ትከተላለች" ሲሉ አምባሳደር ሀሰን ሀሚድ ሀሰን ለስፑትኒክ ተናግረዋል፡፡
በጄኔቫ የሱዳን ቋሚ የዲፕሎማሲ ተልዕኮ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሩሲያ ተልዕኮ ጋር በቅርበት እየሠራ እንደሚገኝም አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡
የሱዳን ግጭት ቢቀጥልም በሞስኮ የሩሲያ-ሱዳን የሚኒስትሮች የጋራ ስብሰባ መካሄዱን እና የከፍተኛ ልዑካን ጉብኝት መደረጉን በማንሳት መደሰታቸውን ገልጸዋል።
አምባሳደር ሀሰን አክለውም የዲፕሎማሲያዊ ህይወት ጉዟቸውን ወደ ሞስኮ በሚሰጣቸው ሹመት ማጠናቀቅ እንደሚፈልጉ ጠቁመዋል።
በሱዳን የሩሲያ አምባሳደር አንድሬ ቼርኖቮል፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ለተራዘመ ግዜ በቀጠለው ወታደራዊ ግጭት ውስጥም ቢሆን እየተፋጠነ ነው ሲሉ ቀደም ብለው አረጋግጠዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X