ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምታቀርበው የምግብ ወጪ ንግድ መጠን በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ100 በመቶ በላይ ጨመረ

ሩሲያ ወደ አፍሪካ የምታቀርበው የምግብ ወጪ ንግድ መጠን በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ100 በመቶ በላይ ጨመረ
ይህ የተገለፀው በአዲስ አበባ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የጋራ ስብሰባ ላይ ነው፡፡ መድረኩ የሩሲያ የፌዴራል ግብርና ኤክስፖርት ልማት ማዕከል (አግሮኤክስፖርት) ኃላፊ ኢሊያ ኢሊዩሺ፣ የሩሲያ ምክትል የግብርና ሚኒስትር አንድሬይ ራዚን እና የሩሲያ አፍሪካ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኢሪና አብራሞቫን አሳትፏል፡፡ ኢሊያ ኢሊዩሺን በዚህ ወቅት ሩሲያ ወደ አፍሪካ ሀገራት የላከቻቸው የግብርና ምርቶች መጠን በ2024 ወደ 7 ቢሊዮን ዶላር እንደደረሰ ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል የግብርና የንግድ ልውውጥ በ18 በመቶ ማደጉንና ስንዴም በ26 ሚሊዮን ቶን የምርት ሽፋን የወጪ ንግድ ዋነኛ ማዕከል ሆኖ መቆየቱን የሩሲያ ምክትል የግብርና ሚኒስትር አንድሬይ ራዚን፤ የአፍሪካን የምግብ ዋስትና ማሳደግ ላይ ባተኮረው ዝግጅት ላይ ተናግረዋል።
እንደ ራዚን ገለጻ፤ 1.3 ሚሊዮን ቶን ገብስ፣ ከ200 ሺ ቶን በላይ በቆሎ እና 35 ሺ ቶን ምስር ሌሎች ጉልህ አቅርቦቶች ናቸው።
ከእህል ውጭ ያለው የምርት አቅርቦት ዓይነት ጭማሬ በጉልህ የሚጠቀስ ነው፦
የአትክልት ዘይት ወጪ ንግድ ወደ 720 ሚሊዮን ዶላር መድረስ በእጥፍ አድጓል።
የተዘጋጁ ምግቦች ጭነት ዋጋ በ51 በመቶ ጨምሯል።
የእንስሳት ምርቶች ወጪ ንግድ በአራት እጥፍ አድጓል።
ቀደም ሲል 200 ሺ ቶን የነበረውን ዓመታዊ የዓሳ ወጪ ንግድ መጠን ለመመለስ ጥረቶች በመካሄድ ላይ ናቸው።
እንደ አግሮኤክስፖርት ገለጻ፤ ሩሲያ የትብብር ማዕቀፎችን ለማጠናከር እና የንግድ ልማትን ለማመቻቸት በ10 የአፍሪካ ሀገራት የግብርና አታሼዎችን መድባለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


