ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ከቡድን 20 ስብሰባ ጎን ለጎን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድረጉ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ከቡድን 20 ስብሰባ ጎን ለጎን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድረጉ
ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ከቡድን 20 ስብሰባ ጎን ለጎን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.11.2025
ሰብስክራይብ

ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባብዌ ከቡድን 20 ስብሰባ ጎን ለጎን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አድረጉ

ምክትል ፕሬዝዳንት ፖል ማሻቲሌ ጆሃንስበርግ ውስጥ የዚምባብዌን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የቀድሞው ጄኔራል ዶ/ር ኮንስታንቲን ቺዌንጋን ማግኘታቸውን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አስታወቋል።

"ደቡብ አፍሪካ በቅርቡ በተካሄደው የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ጉባዔ ላይ ጊዜያዊ ሊቀመንበርነት ስትረከብ ዚምባብዌ ላደረገችው ድጋፍ በድጋሚ ላመሰግን እፈልጋለሁ" ሲሉ ማሻቲሌ ከውይይቱ በኋላ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሁለቱ ሀገራት ከአፓርታይድ እና ከቅኝ አገዛዝ ትግል ጀምሮ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር እንዳላቸው ያስታወሰው የፕሬዝዳንት ፅ/ቤቱ፤ ዚምባብዌ ከደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ዋነኛ የንግድ አጋሮች አንዷ መሆኗን አፅንዖት ሰጥቷል።

በተጨማሪም ከ120 በላይ የደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች በማዕድን ማውጣት፣ በባንክ አገልግሎት፣ በቱሪዝም፣ በንግድ፣ በግንባታ እና ሌሎችም ዘርፎች በዚምባብዌ እንደተሰማሩ ተጠቅሷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0