የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ወታደራዊ የምስራቅ አፍሪካ ፌዴሬሽን እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ
19:55 21.11.2025 (የተሻሻለ: 20:04 21.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ወታደራዊ የምስራቅ አፍሪካ ፌዴሬሽን እንዲመሰረት ጥሪ አቀረቡ
እርምጃው የክልሉን የመከላከያ አቅም በማጠናከር ደህንነቱን እና ለፀጥታ ስጋቶች ምላሽ የመስጠት አቅሙን ያረጋግጣል ሲሉ ሙሴቬኒ ተናግረዋል፡፡
ርዕሰ ብሔሩ በተጨማሪም የውጭ ሀገራት በታሪክ የአፍሪካ ሀገራትን በቀላሉ እንዴት እንደወረሩ በመጥቀስ በብዙ አፍሪካ ሀገራት ደካማ ወታደራዊ አቅም ዙሪያ ስጋታቸውን አንስተዋል።
“አፍሪካን አሁን ማን ሊያድናት ይችላል? ማን ይችላል? ከዚህ ቀደም ሊቢያ በውጭ ኃይሎች ስትጠቃ እዚሁ ቁጭ ብለን ስንመለከት ነበር፤ ስለዚህ መፃኢ ዕድላችንን ለማረጋገጥ የምዕራብ አፍሪካን የፖለቲካዊ ጥምረት ሂደት ተመልክተን፤ ትምህርት ልንወስድ ይገባል” ብለዋል፡፡
ፌዴሬሽኑ የኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ወታደራዊ ኃይሎችን እንደሚያቅፍ አመልክተዋል፡፡
የፕሬዝዳንቱ ሀሳብ የቀጣናው መሪዎች በምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ውስጥ ጥልቅ ውህደትን ለመፍጠር ጥረታቸውን በቀጠሉበት ወቅት የመጣ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X