የማሊ መንግሥት የነዳጅ ታንከሮች ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት በጉምሩክ የሚኖራችውን ቆይታ ከ72 ወደ 24 ሰዓታት ሊቀንስ ነው
19:39 21.11.2025 (የተሻሻለ: 19:44 21.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የማሊ መንግሥት የነዳጅ ታንከሮች ወደ ሀገር ውስጥ ለመግባት በጉምሩክ የሚኖራችውን ቆይታ ከ72 ወደ 24 ሰዓታት ሊቀንስ ነው
የሂደቱን ግዜ መቀነስ "ጣቢያዎችን በፍጥነት ለማጽዳት፣ የታንከሮችን ቀጣይነት ያለው ፍሰት ለማረጋገጥ እና እያንዳንዱ የነዳጅ ጠብታ ያለ መዘግየት ተጠቃሚዎች ጋር እንዲደርስ ዋስትና ይሰጣል" ሲሉ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሙሳ አላሳኔ ዲያሎ ከነዳጅ ኦፕሬተሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።
ነዳጅ በመደበኛነት ወደ ሀገሪቱ እየገባ እና በቂ መጠን ቢኖርም "በነዳጅ ማደያዎች ወረፋው እየጨመረ ነው" ሲሉም አክለዋል።
በሚኒስቴሩ መግለጫ መሠረት መዘግየቶች የተከሰቱት “ለሥራዎች ማነቆ በሆነው የአስተዳደር ችግር” ምክንያት ነው።
“ይህ መዋቅራዊ ለውጥ ሥራ ላይ ሲውል በአንዳንድ የአገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሚታዩትን ረጅም ወረፋዎች በቀጥታ በመቅረፍ ለተጠቃሚዎች ፈጣን እፎይታ ይሰጣል።”
የማሊ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነዳጅ ቀውሱ “የሕዝብ አመፅ ለመቀስቀስ” ዓላማ ባላቸው ያልተጠቀሱ አካላት “ሰው ሠራሽ በሆነ መንገድ” እንደተፈጠረ ቀደም ሲል ገልጸው ነበር።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X