ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ 'የእጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ' አካሄዶችን ለመመከት 'የእኩል አጋርነትን' እያዳበሩ ነው - የሩሲያ አምባሳደር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ 'የእጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ' አካሄዶችን ለመመከት 'የእኩል አጋርነትን' እያዳበሩ ነው - የሩሲያ አምባሳደር
ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ 'የእጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ' አካሄዶችን ለመመከት 'የእኩል አጋርነትን' እያዳበሩ ነው - የሩሲያ አምባሳደር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 21.11.2025
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ደቡብ አፍሪካ 'የእጀ ዙር ቅኝ አገዛዝ' አካሄዶችን ለመመከት 'የእኩል አጋርነትን' እያዳበሩ ነው - የሩሲያ አምባሳደር

የውጭ ተዋናዮች ሚዛናዊ ባልሆኑ የብድር ሥርዓቶች እና የሀብት ተደራሽነት ውሎች አማካኝነት የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊ ጥገኝነት እያስቀጠሉ ነው ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሩሲያ አምባሳደር ሮማን አምባሮቭ ለስፑትኒክ በሰጡት ቃለምልልስ ላይ ተናግረዋል፡፡

ዲፕሎማቱ ሞስኮ ከፕሪቶሪያ ጋር የምታደርገውን ትብብር በቅድመ ሁኔታዊ ድጋፎች ላይ ያልተመሠረተ፤ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ እና "ከቅኝ አገዛዝ አካሄዶች" ተቃራኒ ሞዴል አድርገው ገልጸውታል።

በአምባሳደር አምባሮቭ የተብራሩት ዋና ዋና የትብብር መስኮች፦

ንግድና ኢንቨስትመንት፦ የደቡብ አፍሪካ ባለሥልጣናት በተለይም በኃይል፣ በግብርና፣ በማዕድንና በማዕድን ሀብት አቅርቦት ላይ የሰፋ ንግድና ኢንቨስትመንት ይፈልጋሉ፣

የሕዋ ትብብር፦ የሕዋ ትብብር በሁለትዮሽ እና በብሪክስ ማዕቀፎች ውስጥ እያደገ የመጣ ሲሆን ሞስኮ ለአፍሪካ አጋሮች የምድር መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ለማስፋት አቅዳለች፣

የኃይል ውይይት፦ በቀጥተኛ የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ንግግሮች ዙርያ ምንም አስተማማኝ የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም ደቡብ አፍሪካ ለጋዝ መፍትሄዎች ያላት ፍላጎት ይህንን "አስቻይ እና መልካም" ሊያደርገው እንደሚችል አምባሳደሩ ገልፀዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0