ዛምቢያ እና ታንዛኒያ ድንበር ተሻጋሪ የባቡር መሠረተ ልማትን ለማሻሻል ከቻይና ጋር ስምምነት ተፈራረሙ
19:03 21.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 21.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ዛምቢያ እና ታንዛኒያ ድንበር ተሻጋሪ የባቡር መሠረተ ልማትን ለማሻሻል ከቻይና ጋር ስምምነት ተፈራረሙ
ታሪካዊው የ1.4 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት፤ የባሕር በር የሌላት ዛምቢያን በህንድ ውቅያኖስ ካሉ የታንዛኒያ ወደቦች ጋር የሚያገናኘውን ስትራቴጂካዊ የታዛራ የባቡር መስመር ሙሉ በሙሉ ለማዘመን ያለመ መሆኑን የዛምቢያ ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ ተናግረዋል፡፡
ስምምነቱ ለቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ከ28 ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን ጉብኝት ያደረጉት ሊ ቺያንግ በተገኙበት ተፈርሟል፡፡
"የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ ታዛራን ለማነቃቃት በተካሄደው የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘታቸው ክብር ተሰምቶኛል። ይህ በየብስ ለተከበበችው ዛምቢያ ራዕይ የ1.4 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ነው" ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገፃቸው ላይ ጽፈዋል፡፡
የባቡር መስመሩ ማሻሻያ ዓላማ አሁን ያለውን 100 ሺህ ቶን የጭነት አቅም በዓመት ከ2.4 ሚሊዮን ቶን በላይ ማሳደግ፣ የሥራ ዕድል መፍጠር እና የቀጣናዊ ንግድን ማሳደግ እንደሆነ ሂቺሌማ ገልጸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ የ1,860 ኪሎ ሜትር ሀዲዶችን፣ ጣቢያዎችን፣ ድልድዮችን እና ዋሻዎችን ጨምሮ የባቡር መስመሩን መልሶ ማቋቋም እንዲሁም አዲስ የሚንቀሳቀስ ባቡር መግዛትን እንደሚያካትት ተዘግቧል፡፡
በመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተሳተፉት የታንዛኒያ ምክትል ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ንቺምቢ፤ ዘመናዊ የታዛራ የባቡር መስመር የደቡባዊ አፍሪካን ግብርና፣ ማዕድን እና ኢንዱስትሪ ያነቃቃል ብለዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X


