የምዕራባውያን ሥርዓተ ትምህርት ዋነኛ ዓላማ የተማረ የሰው ኃይል ከሀገራት ማስኮብለል ነው - የሩሲያ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊ

ሰብስክራይብ

የምዕራባውያን ሥርዓተ ትምህርት ዋነኛ ዓላማ የተማረ የሰው ኃይል ከሀገራት ማስኮብለል ነው - የሩሲያ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ትብብር ኤጀንሲ ኃላፊ

ኢቭጌኒ ፕሪማኮቭ፤ አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ለአፍሪካውያን የሚሰጧቸው የትምህርት ዕድሎች፤ ብሩህ አዕምሮ ያላቸው ወጣቶችን በምቾት ፍለጋ በወጡበት የሚያስቀር መሆኑን ይናገራሉ።

ኃላፊው ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሩሲያ በትምህርት ዘርፉ የምትከተለው አካሄድ ከዚህ የተለየ መሆኑን በማንሳት፤ አፍሪካውያን ተማሪዎች ወደመጡበት ተመልሰው ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ እንደምታበረታታ ገልጸዋል።

"ከአፍሪካ የሚሄዱ ባለ ብሩሕ አዕምሮዎች በምዕራቡ ዓለም ምናልባት ሕይወታቸውን ከማሻሻል የዘለለ ተፅዕኖ ሊኖራቸው አይችልም። ከሶቪየት ኅብረት ጊዜ አንስቶ እኛ ዕውቀት ያካፈልናቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ግን ማኅበረሰባቸውን በተለያዩ ዘርፎች በማገዝ ላይ ናቸው" ብለዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0