የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቡድን 20 ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ጆሀንስበርግ ገቡ
17:07 21.11.2025 (የተሻሻለ: 17:24 21.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቡድን 20 ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ጆሀንስበርግ ገቡ
"ከዓለም መሪዎች ጋር በቁልፍ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይቶችን እንደማደርግ ተስፋ አደርጋለሁ። ትኩረታችን ትብብርን ማጠናከር፣ የልማት ቅድሚያዎችን ወደ ፊት ማስኬድ እና ለሁሉም የተሻለ የወደፊት ዕድል ማረጋገጥ ላይ ይሆናል" ሲሉ ናሬንድራ ሞዲ በኤክስ ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
የ2025ቱ ስብሰባ በአፍሪካ አህጉር ላይ የሚካሄደው የመጀመሪያው የቡድን 20 የመሪዎች ስብሰባ መሆኑ "በተለየ ሁኔታ ልዩ" ያደርገዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀደም ብለው ተናግረዋል።
ሞዲ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉብኝታቸው፦
"አንድ ምድር፣ አንድ ቤተሰብ፣ አንድ መፃኢ እድል" የሚለውን የህንድ ራዕይ ለቡድን 20 የመሪዎች ስብሰባ ተሳታፊዎች ለማቀረብ፣
በ6ኛው የህንድ፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካ የውይይት መድረክ ላይ ለመሳተፍ፣
ከህንድ ውጭ ከፍተኛ የህንድ ዲያስፖራዎች በሚገኙባት ደቡብ አፍሪካ፤ ከማሕበረሰቡ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ለመወያየት አቅደዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

