ሱዳናውያን አማጺው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለመመከት አገር አቀፍ ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ከፍተኛ አዛዡ ጥሪ አቀረቡ
19:10 20.11.2025 (የተሻሻለ: 19:24 20.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሱዳናውያን አማጺው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ለመመከት አገር አቀፍ ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ከፍተኛ አዛዡ ጥሪ አቀረቡ
የብሉ ናይል የአየር መከላከያ ዘርፍ አዛዥ አሊ ሐሰን ቤሎ፣ ይህንን ጥሪ ያቀረቡት የሱዳን ጦር ኃይሎች ዋና አዛዥ አብደል ፈታሕ አል-ቡርሃን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችውን አል-ፋሸርን ከተቆጣጠሩ በኋላ ሕዝቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ላቀረቡት የቅርብ ጊዜ ጥሪ ምላሽ ነው።
የጦር አዛዡ ሱና በተባለው የመንግሥት ዜና ወኪል አማካኝነት ባስተላለፉት መግለጫ በኮርዶፋን ክልል የተገኙትን የቅርብ ጊዜ ወታደራዊ ስኬቶች አወድሰዋል።
“አሁንም በከበባ ውሰጥ ባሉ ከተሞች ድል አይቀሬ ነው” ሲሉ የሱዳን ወጣቶች የአል-ቡርሃንን ጥሪ እንዲቀበሉ አሳስበዋል።
ይህ የቅስቀሳ ዘመቻ የሚካሄደው ኡም-ሰያላን እና ሌሎች ስልታዊ ቦታዎችን ጨምሮ በበርካታ የኮርዶፋን አካባቢዎች ሠራዊቱ ድል ማድረጉን በሚያሳዩ ሪፖርቶች መካከል ነው።
ሠራዊቱ “አገሪቱ ከአመፅ እና ከውጭ አጀንዳዎች እስክትጸዳ ድረስ” በአማፂያኑ ላይ የሚያካሂደውን ዘመቻ እንደሚቀጥል ቃል ገብቷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X