ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል አገራት ግብርና ሰፊ ተሞክሮ ትወስዳለች - የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል አገራት ግብርና ሰፊ ተሞክሮ ትወስዳለች - የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት

ኢትዮጵያ እንደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድ እና ብራዚል ያሉ አገራትን ልምድ በመቀመር ጠንካራ የግብርና ኢኮኖሚ ለመፍጠር እየሠራች መሆኑን በኢንስቲትዩቱ የግብርና ኮሜርሻላይዜሽን ክላስተር ዋና ዳይሬክተር ዳኛቸው ሉሌ (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"ሕንድ እና ቻይና መሠረታቸው ግብርና ነበር። ሩሲያ እና ብራዚልም በግብርና ኢኮኖሚያቸውን አጠናክረዋል። የአባል አገራቱ ተሞክሮ በምግብ ራሳችንን ለመቻል ለምናደርገው ጥረት ትልቅ ግብዓት ነው።" ብለዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፣ አገራቱ በተለይ በስንዴ እና ሩዝ ምርት ላይ ያሳዩትን እመርታ ኢትዮጵያ በተለያዩ ሰብሎች ላይ ለመድገም እንደምትሠራም አመላክተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0