"በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች" - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች" - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ
በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.11.2025
ሰብስክራይብ

"በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች" -  የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ

ሩሲያን አስመልክቶ በዋና ዋናዎቹ ሚዲያዎች አማካይነት አፍሪካ ውስጥ ይተላለፍ የነበርው መረጃ፣ በምዕራባውያን ሚዲያዎች ፍላጎት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ 'የተበላሸ' ነው ብሎ መናገር ይቻላል ሲሉ አሌክሳንደር ሽፒን ገልፀዋል፡፡

"ጉዳቱ በሩሲያ ላይ ብቻ የተወሰነ አልነበረም። በአፍሪካ እና በመላው ዓለም ላይ የደረሰ ነው። ትክክለኛ መረጃ የማንኛውም ንግድ መሠረት ብቻ አይደለም፤ የልማት መሠረት ነው።" ሲሉ ይተላለፉ የነበሩት መረጃዎች የተደበላልቁ እና ከእውነታ የራቁ ጭምር መሆናቸውን በአፍሪካ አገራት የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ጎን ለጎን “የምግብ ሉዓላዊነት የመረጃ ገጽታ፤ ሚዲያዎች ቢዝነሶች በአፍሪካ እንዲሠሩ ማድረግ ላይ ያላቸው ሚና” በሚል ርዕስ በተደረገው የፓናል ውይይት ላይ ተናግረዋል፡፡

ስፑትኒክ አፍሪካ ይህንን ውዥንብር ለማጥራት የውሸት ምስሎችን መፍጠር ሳያስፈለግው እና ማንንም ጣልቃ ሳያስገባ በቀጥታ እየሠራ መሆኑን አሰታውቀዋል፡፡ 

የስፑትኒክ አፍሪካ ሥራ በሞስኮ ቢሮ ብቻ ሳይገደብ፣ አዲስ አበባን ጭምሮ በዘጠኝ የአፍሪካ አገራት ውስጥ ቅርንጫፎችን በመከፈት በተለያዩ የየአካባቢው ቋንቋዎች እየሠራ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡ 

"ስፑትኒክ የሚሠራው እኔን ብቻ ስሙኝ እያለ አይደለም። ይልቁንም በዋነኝነት ውይይት ላይ ነው። በባሕሎቻችን መካከል የሚደረግ ውይይት። ዝም ብለን አንናገርም፤ እናዳምጣለን፣ እንሳተፋለን። [...] እኛ ስለ ሩሲያ አይደለም የምንናገረው፤ ስለ አፍሪካ እንጂ። በትክክል ስናስቀምጠው ደግሞ፣ በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች። በእርግጥም፣ ይህ ሁሉ ሩሲያን እንድናሳይ ያስችለናል። ምክንያቱም እኛ ምን ያህል የአፍሪካ ጉዳይ ግድ እንደሚሰጠን ያመላክታል።" ብለዋል።

🟠 በፓናሉ፣ ሚዲያዎች ቢዝነሶች አፍሪካ ውስጥ አጋሮችን እንዲያገኙ በምን መልኩ ማገዝ፣ መተማመንን መፍጠር እና ሐሰተኛ ዜናዎችን መዋጋት እንዳለባቸው ውይይት ተድርጓል፡፡ 

🟠 ተወያዮቹ፣ ቀድሞም በአፍሪካ ውስጥ በሚሠሩ የሩሲያ ኩባንያዎች ልምድ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት፣ የኮሙኒኬሽን እና የሚዲያ ፕሮጄክቶችን እንዴት እንደሚተገብሩ፣ ስማቸውን እንደሚገነቡ እና በአኅጉሪቱ ስላሏቸው ተነሳሽነት ሐሳቦቻቸውን አጋርተዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ
1/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ
2/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ
3/4
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
በስፑትኒክ አፍሪካ፣ አኅጉሪቱ ራሷ ስለ አፍሪካ ትናገራለች - የስፑትኒክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ኃላፊ - Sputnik አፍሪካ
4/4
1/4
2/4
3/4
4/4
አዳዲስ ዜናዎች
0