"የዓለም አቀፉን የገንዘቡ ተቋም ፕሮግራም ስትቀበል፣ የራስህን ፖሊሲ እያስረከብክ ነው" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ
16:40 20.11.2025 (የተሻሻለ: 16:44 20.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
"የዓለም አቀፉን የገንዘቡ ተቋም ፕሮግራም ስትቀበል፣ የራስህን ፖሊሲ እያስረከብክ ነው" ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገዳ
ከአይኤምኤፍ ጋር ስትዋዋል ሁሉንም የማክሮ ፖሊሲ መሥሪያ አቅምህን፣ ፊስካል ፖሊሲህንም ታስረክባለህ ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ፕሮፌሰር የሆኑት ዓለማየሁ ገዳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ዓለም ባንክና አይኤምኤፍ አፍሪካ ውስጥ በገቡባቸው አገራት ሁሉ የመንግሥት ወጪ ላይ ከፍተኛ ቁጠባ (austerity) እንዲተገብሩ ያዝዛሉ ሲሉ ተችተዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ፣ "በቅርቡ በኢትዮጵያ፣ በጋና፣ በናይጄሪያ፣ በዛምቢያ፣ በኬንያ እና በግብፅ አድርገውታል። እነዚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው። በእነዚህ አገራት ሁሉ ፖሊሲው ተመሳሳይ ነው። ሆኖም አገራቱ ፈጽሞ የተለያዩ ናቸው" በማለት ለአገራት የሚመከርው ፖሊሲ ወጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ዓለማየሁ አክለውም የገንዘብ ተቋማቱ የሚተገብሯቸው የመዋቅር ማስተካከያ ፖሊሲዎች ወይም “የዋሽንግተን ኮንሰንሰስ” ትግበራዎች ውጤትን ጠቅሰዋል፡፡
"ይህ በአፍሪካ በ1980ዎቹና በ1990ዎቹ ተተግብሯል። በዚያን ጊዜ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጥልቅ ጥናት አድርጎ፣ በዚህ ፖሊሲ ምክንያት በአፍሪካ አገሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ አረጋግጧል። በአማካይ የዕድገት መጠኑም አሉታዊ ነበር።"
በሰው ሠራሽ አስተውሎት የበለጸገ ምስል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X