"የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም" - የግብርና ሚኒስትር

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ"የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም" - የግብርና ሚኒስትር
የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም - የግብርና ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ, 1920, 20.11.2025
ሰብስክራይብ

"የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም" - የግብርና ሚኒስትር

ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ፣ የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ ይልቁንም "የክብር እና የነጻነት ጉዳይ ነው" ሲሉ በሩሲያ እና በኢትዮጵያ መንግሥታት በጋራ አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀውና እስከ ነገ በሚቆየው የአፍሪካ አገራት የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ፣ "አፍሪካ በራሷ ሀብት፣ አቅምና መንገድ ህዝቧን መመገብ መቻል አለባት፡፡ ...ኢትዮጵያ በበጋ ስንዴ ፕሮጄክት ፍላጎቷን ከማሟላት ባለፈ ከስንዴ አስመጪነት ተላቅቃ ወደ ውጭ ለመላክ ወደሚያስችላት ምዕራፍ እየተሸጋገረች ትገኛለች፡፡” ሲሉ የኢትዮጵያን ተሞክሮ አጋርተዋል፡፡

አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የምትሄድበት መንገድ በትብብርና ቅንጅት ላይ ተመሥርቶ የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናን ታሳቢ ማድረግ እንዳለበትም አጽናኦት መስጠታቸውን በስፍራው የሚገኘው የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

ጉባኤው ላይ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴሬኪን፣ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማኅበር፣ የአፍሪካ ሕብረት ልዑካን መሪ ብሩስ ሎሬንዞ ቢበር እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተወካዮች፣ ተመራማሪዎችና ምሁራን ተገኝተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም - የግብርና ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ
1/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም - የግብርና ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ
2/3
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
የምግብ ሉዓላዊነት ጉዳይ ለአፍሪካ የምርታማነት ጉዳይ ብቻ አይደለም - የግብርና ሚኒስትር - Sputnik አፍሪካ
3/3
1/3
2/3
3/3
አዳዲስ ዜናዎች
0