ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸውን ብርቱ ወዳጅነት በሥራዬ አይቻለሁ - ዕውቁ ቅርስ ሰብሳቢ

ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ ያላቸውን ብርቱ ወዳጅነት በሥራዬ አይቻለሁ - ዕውቁ ቅርስ ሰብሳቢ

ዐብዲ ነጋሽ፣ ለሦስት አስርት ዓመታት  ለሚጠጋ ጊዜ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚዘክሩ ልዩ ልዩ ቅርሶችን በመሰብሰብ ላይ ይገኛል።

ቅርስ ሰብሳቢው በሥራው የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ጥብቅ ትስስር የሚያሳዩ መጻሕፍትን፣ ፎቶዎችን፣ የሙዚቃ ሸክላዎችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ከማግኘት ባሻገር፤ ለአገራቱ የደም ትስስር ሕያው ማሳያ የሆኑ ደንበኞች እንደሚገጥሙትም ያነሳል።

"ብዙ ሩሲያኛ የሚችሉ ኢትዮጵያውያን አሉ። በወታደራዊ መንግሥት ጊዜ በርካቶች ወደ ሶቪዬት ሕብረት ሄደው ከመማራቸው ጋር የተያያዘ ይመስለኛል፡፡ በተመሳሳይም አማርኛ አሳምረው የሚናገሩ በትዳር ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚኖሩ ሩሲያውያንም አገኛለሁ፡፡ እንደዚህ አይነቱ ነገር ከሌሎች አገራት ጋር በብዛት አይገጥመኝም።" ብሏል።

ዐብዲ ነጋሽ ከ1950 ጀምሮ ስለታተሙ የሩሲያ-አማርኛ መዝገበ ቃላት እና ሌሎች መጻሕፍት በተመለከተ ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0