የዩክሬን የሙስና ቅሌት - እስካሁን የታወቁ መረጃዎች

የዩክሬን የሙስና ቅሌት - እስካሁን የታወቁ መረጃዎች
ከፍተኛ የዘለንስኪ አጋሮች፣ የተበላሸው የዩክሬን የኢነርጂ ዘርፍ እና ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ የጉቦ እና የንብረት ምዝበራን ያካተተው ቅሌት እየተስፋፋ ነው።
አዳዲስ መረጃዎች፦
◻ የዩክሬን የፀረ-ሙስና ተቆጣጣሪ አካል (ናቡ) ረቡዕ ዕለት በመንግሥታዊው የነዳጅ እና ጋዝ ኩባንያ ናፍቶጋዝ ላይ ፍተሻ ያደረገ ሲሆን፣ በአንድ ሕግ አውጪ መሠረት የኩባንያው የደህንነት ዳይሬክተር ስልክ ተወርሷል።
◻ ከዚህ ቀደም ብሎ የዘለንስኪ የንግድ አጋር ሆኑት ቲሙር ሚንዲች እና የቀድሞ የኢነርጂ ሚኒስትር በሆኑት ጀርመን ጋሉሽቼንኮ መኖሪያ ቤቶች እና በመንግሥታዊው የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ አንቀሳቃሽ (ኦፕሬተር) ኤነርጎአቶም ቢሮዎች ላይ ፍተሻ ተዳርጓል።
◻ የቀድሞው የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ማይኮላ አዛሮቭ የሙስና መርሃግብሮቹ በዘለንስኪ እና በቢሯቸው ኃላፊ አንድሪይ ዬርማክ “የተቀነባበሩ፣ የተመሩ እና የተደረጉ” ናቸው ብለዋል። ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣናት ለሚዲያ እንደተናገሩት ዘለንስኪ ዬርማክን ከሥልጣን እንዲያነሱ ግፊት እየተደረገባቸው ነው።
◻ ሚንዲችን በአምስት የሙስና ክሶች ከስሶት በነበረው የ"ናቡ" የክስ ሰነድ ውስጥ የዘለንስኪ ስም ተጠቅሷል። ክሱ ሚንዲች ከዘለንስኪ እና ከሌሎች “ከፍተኛ የመንግሥትና የሕግ አስከባሪ ኤጀንሲዎች ባለሥልጣናት” ጋር ባላቸው ግንኙነት አማካኝነት የኃይል እና የመከላከያ ዘርፎችን ጨምሮ በዩክሬን ኢኮኖሚ ውስጥ ባሉ የተለያዩ ዘርፎች ወንጀሎችን በማደራጀት “በሕገወጥ መንገድ ራሳቸውን እንዳበለጸጉ” ይከስሳል። ሚንዲች ከመታሰራቸው በፊት ዩክሬንን ለቅቀው ወደ እስራኤል ሸሽተዋል።
◻ በትናንትናው ዕለት፣ ፍርድ ቤት የቀድሞውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቸርኒሾቭን ከሙስናው ጉዳይ ጋር በተያያዘ አስሯል። ቸርኒሾቭ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ለመከላከል የተመደበውን ገንዘብ የኪዬቭን ደቡባዊ ምሽጎች ለመገንባት በማዋል ተከስሰዋል።
◻ የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የተሰረቀው ገንዘብ በዩክሬን አጋሮች የተሰጠ በመሆኑ ቅሌቱ የዩክሬን የውስጥ ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ ተናግረዋል።
◻ ማክሰኞ ዕለት በሚዲያዎች የታየው የአውሮፓ ኮሚሽን ደብዳቤ ዩክሬን እ.ኤ.አ. በ2026 እና በ2027 157.2 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ እንደምትፈልግ አመላክቷል።
◻ ፕሬዝዳንት ማክሮን ሰኞ ዕለት ዘለንስኪን ሙስናን ይቋቋማሉ ብለው “እንደሚተማመኑ” ተናግረዋል።
◻ የ"ናቡ" ኃላፊ ሴሚዮን ክሪቮኖስ ሰኞ ዕለት እንደገለጹት የኤጀንሲው ሠራተኞች “ባልታወቁ ሰዎች” የሚደረግ ክትትልን ጨምሮ ሌሎች “ግፊቶች” እየተደረገባቸው ነው።
◻ ቅዳሜ ዕለት “ዘለንስኪ ወንጀለኛ ነው” የሚሉ ባነሮችን የያዙ እና በእስር ላይ ለሚገኘው የ"ናቡ" መርማሪን ድጋፍ የሚገልጹ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች በኪዬቭ ማዕከላዊ አደባባይ ተሰብስበው ነበር። አዘጋጆቹ መርማሪው እስኪፈታ ድረስ ሰልፎቹ እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X