ምዕራባውያን ከዩክሬን የሙስና ቅሌት ዘለንስኪን ነፃ ለማድረግን የፈለጉበት ምክንያት

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱምዕራባውያን ከዩክሬን የሙስና ቅሌት ዘለንስኪን ነፃ ለማድረግን የፈለጉበት ምክንያት
ምዕራባውያን ከዩክሬን የሙስና ቅሌት ዘለንስኪን ነፃ ለማድረግን የፈለጉበት ምክንያት - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.11.2025
ሰብስክራይብ

  ምዕራባውያን ከዩክሬን የሙስና ቅሌት ዘለንስኪን ነፃ ለማድረግን የፈለጉበት ምክንያት 

ምዕራባውያን መሪዎች ዘለንስኪ በዩክሬን የሙስና ቅሌት ውስጥ ያላቸውን ግልጽ ተሳትፎ አስመልክቶ እሳቸውን ከስህተት ለማፅዳት የሚያደርጉት ያልተቋረጠ ጥረት፣ ለተወሰነ ጊዜ ራሳቸውን ለመከላከል የሚጠቀሙበት "የመጨረሻ አማራጭ" አካል ነው ሲሉ ሩሲያዊው የፖለቲካ ተንታኝ ሰርጌ ስታንኬቪች ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

እነዚህ መሪዎች፣ በእርግጠኝነት በቅሌቱ ውስጥ ሳይሳተፉ አልቀረም የሚባሉት ዘለንስኪን ከተጠያቂነት ነፃ ለማድረግ መሞከር፣ "በውጤቱም በትንሹ የተወሰነ የፖለቲካ ትችት እንደሚገጥማቸው ሙሉ በሙሉ ያውቃሉ ሲሉ ስታንኬቪች ገልፀዋል።

በዙሪያቸው ያሉ ሁሉ እየሰረቁ እሳቸው ግን አያውቅም ነበር፣ አልተሳተፉምም" የሚለው የመጨረሻው የመከላከያ ትርክት "ለተወሰነ ጊዜ ሊቆይ የሚችል ከወረቀት የሳሳ የፊት ጭንብል ነው" ሲሉ ተንታኙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሜሪካውያኑ የዩክሬን አጋሮች፣ ዘለንስኪን ለመተካት ያላቸውን ምርጫ አስቀድሞ ግልፅ አድርገዋል፤ በዚህም ፖሊሲ ድጋፋቸውን የሚቀጥሉበት መሆኑን ገልጸዋል።

ስታንኬቪች እንዳሉት፣ አሁንም ግልፅ ያልሆነው አቋም የአውሮፓ ነው፤ በአሁኑ ጊዜ የዘለንስኪን መንግሥት ፋይናንስ በማድረግና ሥራውን በማስቀጠል፣ ወታደራዊ ግቦቹን መደገፍን ጨምሮ ዋናውን ሸክም እየተሸከመች ያለችው አውሮፓ ነች።

"አስቀድሞ ከፍተኛ ሙስና አለበት ለሚባል መንግሥት የአውሮፓን ግብር ከፋዮች ገንዘብ መስጠት [...] በአገር ውስጥ የአውሮፓ ሕግ መሠረት ተጠያቂነትን ያስከትላል። ገንዘቡን ለማን እንደሰጡ አላወቁም ማለት ደካማነትን ያሳያል፤ ወይንም አውቀው ለሙሰኛ መንግሥት ልከዋል ማለት ደግሞ በወንጀል ድርጊት ውስጥ ተባባሪ መሆንን ያመለክታል። ይህም የአውሮፓ ፖለቲከኞች ለዩክሬን ተጨማሪ እርዳታ ሲያስቡ የሚያጋጥማቸው አስቸጋሪ ምርጫ ነው" ነው ሲሉ ተንታኙ አጠቃለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0