ሩሲያ በውጭ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኔትዎርኮች ጥገኛ ልትሆን አትችልም፤ ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው - ፑቲን
ሩሲያ በውጭ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ኔትዎርኮች ጥገኛ ልትሆን አትችልም፤ ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው - ፑቲን
ፑቲን በ 2025 “ጉዞ ወደ ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ)” ኮንፍረንስ ላይ የሰጧቸው ቁልፍ መግለጫዎች፦
🟠 ሩሲያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ኢንዱስትሪን ለማስተዳደር ማዕከላዊ ዋና መሥሪያ ቤት ያስፈልጋታል፡፡
🟠 በስበርባንክ እና ያንዴክስ የበለፀጉ ምርቶች በዓለም ላይ ካሉት ምርጦች መካከል ናቸው።
🟠 የሩስያ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥርዓቶች እድገት ሙሉ በሙሉ በሩሲያ ስፔሻሊስቶች (ባለሙያዎች) ቁጥጥር ስር መቆየት አለባቸው፡፡
🟠 ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ግዛቶች አሁን የራሳቸውን የየሰው ሠራሽ አስተውሎት ቋንቋ ሞዴሎች ለማዘጋጀት እየተወዳደሩ ነው፡፡
🟠 የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሞዴሎች ለመረጃ ስርጭት በጣም ወሳኝ ከሆኑ መሣሪያዎች ውስጥ አንዱ እየሆኑ ነው እና ቀድሞውኑም በዓለም አቀፍ ሂደቶች ላይ ተጽእኖ እያሳደሩ ይገናሉ፡፡
🟠 ሩሲያ በ”ጄኔሬቲቭ” የሰው ሠራሽ አስተውሎት መስክ የራሷን ሙሉ የቴክኖሎጂ ስብስብ ማዳበር አለባት፡፡
🟠 የጄኔሬቲቭ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎች ለሩሲያ የወደፊት ስልታዊ ናቸው።
🟠 ሩሲያ በሰው ሠራሽ አስተውሎት እድገት ውስጥ ያለማቋረጥ ወደፊት መገስገስ ይገባታል፡፡
🟠 ሩሲያ ብሪክስ እና የሻንጋይ ትብብር ድርጅትን ጨምሮ ከአጋሮቿ ጋር በሰው ሠራሽ አስተውሎት መስክ ዓለም አቀፍ ትብብር ትገነባለች፡፡
🟠 ሩሲያ በትላልቅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫዎች ላይ በመመስረት የመረጃ ማቀነባበሪያ ማዕከላትን መገንባቷ ትቀጥላለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X