ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም
ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም - Sputnik አፍሪካ, 1920, 19.11.2025
ሰብስክራይብ

ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም

በትናትናው ዕለት ይፋ የተደረገው የጤና ወግ የምስራቅ አፍሪካ ዲጂታል መድረክ ወጣቶችን በክህሎት ልማት፣ የሙያ ፍለጋ መሣሪያዎችን እና የእድሎች ተደራሽነትን በማቅረብ የአዲሱን ትውልድ አቅም ለማጎልበት ማሰቡን የፕሮግራሙ ኃላፊ ሶፎኒያስ ግርማ ተናግረዋል።

ሶፎኒያስ ግርማ፣ “መድረካችን በአፍሪካ ቀንድ አራት ዋና ዋና ይፋዊ ቋንቋዎች ተቀርጾና ተዘጋጅቶ ቀርቧል። እነዚህም ፈረንሳይኛ፣ ዐረብኛ፣ እንግሊዝኛ እንዲሁም አማርኛ ናቸው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስዋሂሊን እናጨምራለን” ሲሉ ተደራሽነቱን የማስፋት እንቅስቃሴዎችን ገለጸዋል።

  ኢኒሼቲቩ ባዘጋጀው የዲጂታል መድረክ አማካኝነት እ.ኤ.አ. እስከ 2034 ድረስ 15 ሚሊዮን ወጣቶችን ለማሰልጥን እቅድ መያዙኑም ጨምረው አስረድተዋል፡፡

"ቀደም ሲል የናይጄሪያን ወጣቶች ያሳተፈ የሙከራ ፕሮጀክት ተግባራዊ አድርገናል" በማለት ፕሮግራሙን በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋፋት እቅድ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

እንቅስቃሴውን እ.ኤ.አ. በ2024 የጀመረው የሙያ ወግ ወጣቶች በፍጥነት በሚለዋወጠው የዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ እንዲበለፅጉ የማዘጋጀት ዓላማ መያዙን ኃላፊው ገልጿል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም - Sputnik አፍሪካ
1/2
© telegram sputnik_ethiopia / ወደ ፎቶ ባንክ ይሂዱ
ፕሮጀክቱ በአፍሪካ ደረጃ ለማስፋት ታቅዷል - የሙያ ወግ ፕሮግራም - Sputnik አፍሪካ
2/2
1/2
2/2
አዳዲስ ዜናዎች
0